እንኳን ወደ ማን ሲቲ አዲስ በደህና መጡ

በኢትዮጵያ የማንችስተር ሲቲ ክለብ ይፋዊ የደጋፊዎች ማህበር

በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው ይፋዊ የማንችስተር ሲቲ የደጋፊዎች ማህበር

The club was formed in 2018, by City fans for City fans to be the main hub for Manchester City fans in Addis.

አባል ስንሆን የምናገኛቸው ጥቅማ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

  • እውቅና ያለው የአባልነት መታወቂያ
  • በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሌሎች የሲቲ ደጋፊዎች ጋር በመገናኘት ጨዋታዎችን በአንድ ላይ ማየት
  • የደጋፊ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ሁሉም ዝግጅቶች ላይ መጋበዝ
  • ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መፍጠር
  • በአካል የማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ሄዶ የማየት እና ሌሎች ሰፕራይዝ ጥቅሞች ይኖሩታል።

ከቦርድ አባሎቻችን ጋር ይተዋወቁ

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

የምኖረው ከአዲስ አበባ ውጭ ነው፡፡ የአባልነት መታወቂያ ካርድ እንዴት ማግኘት እችላለው?

ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደጋፊዎች የአባልነት መታወቂያ እየሰጠን ቆይተናል፡፡ የባንክ ሂሳብ አለን፡፡ ክፍያው ከተፈፀመ በኋላ የማንችስተር ሲቲ ይፋዊ መታወቂያ እናዘጋጃለን እና እርስዎ በሚያውቋቸው ሰዎች ወይም በሌላ መንገድ እርስዎ ባሉበት ቦታ እንልክሎታለን፡፡

ክፍያው ለስንት ጊዜ ነው የሚያገለግለው?

የሚያገለግለው ለአንድ አመት ብቻ ነው፡፡ በአመቱ መታወቂያው መታደስ አለበት። ለአንድ የፕሪሚየር ሊግ አመት ብቻ ያገለግላል። ዓመታዊው ክፍያ 200 ብር ብቻ ነው!

ማን ሲቲ አዲስ ከደጋፊ ማህበሩ የሚያገኘው ጥቅም ምንድነው?

ማን ሲቲ አዲስ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ በኢትዮጵያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ውስጥ በህጋዊነት ተመዝግበናል፡፡ የምናገኘው ገቢ የአመታዊ የአባላት ክፍያ ብቻ ነው፡፡ ግባችን ብዙ አባላትን ማግኘት እና በመላው ኢትዮጵያ ሁሉንም የማን ሲቲ ደጋፊዎች ማደራጀትና ማሰባሰብ ነው፡፡ የእኛ ትርፍ እሱ ነው።

ተጨማሪ ጥያቄዎች አሉዎት? እባክዎን ያግኙን

    አዳዲስ ዜናዎችና መረጃዎች

    የማን ሲቲ አዲስ የእውቅና የምስክር ወረቀት

    የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኢጀንሲ ለማን ሲቲ አዲስ የሰጠው የምዝገባ የምስክር ወረቀት

    ይፋዊ የማንችስተር ሲቲ የደጋፊዎች ማህበር የእውቅና ምስክር ወረቀት ከማንችስተር ሲቲ ለማን ሲቲ አዲስ

    ካዛኒቺስ ከጁፒተር ሆቴል አጠገብ ብሉምቴክ ህንሳ 11ኛ ፎቅ

    elias@mancityethiopia.com

    +251912497618

    FOLLOW & LIKE US

    Social media & sharing icons powered by UltimatelySocial