ሰላም እንዴት ናችሁ

Manchester City Fan Club

ሰላም እንዴት ናችሁ

November 3, 2020 Uncategorized 0

ሰላም እንዴት ናችሁ? ማን ሲቲ አዲስ  የበጎ አድራጎት ስራ እንደሚሰራ ይታወቃል። በአሁኑም አመት
ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድ ሁድ ካንሰር ማዕከል ለመርዳት ዕቅድ ይዘናል። በማዕከሉ ከ5 ወር ጀምሮ እስከ 16 ዓመት የሚሆኑ ታማሚ ህጻናት ይገኛሉ። ድጋፍ የሚደርግላቸው በክፍለ ሀገር ለሚኖሩ ወገኖቻችን ሲሆኑ ህክምናው በጥቁር አምበሳ ሆስፒታል የሚካሄድ በመሆኑ ለረጅም ጊዜ አዲስ አበባ ተቀምጠው መከታተል ስለሚከብዳቸው  የመጠለያ የምግብ  የትራንስፖርትና የመድሀኒት  ወጪ  ድጋፍ ይደረግላቸዋል። ህፃናት በመሆናቸው አሳዳጊዎቻቸው አብረው በመጠለያው ይቆያሉ። ፕሮግራማችን የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 12/2013 ዓ.ም ስለሆነ  በእለቱ በመገኘት  አጋርነታችሁን እንደምታሳዩን አንጠራጠርም። በተጨማሪም ላልሰማም በማሰማት ዙሩያችሁ ያለውን ሰው በማስተባበር  ከጎናችን እንድትሆኑ ከአደራ ጋር እናሳስባለን። ድጋፉ በገንዘብም በአይነትም መሆን ይችላል። በአካል መገኘትም በራሱ ድጋፍ ስለሆነ እንድተገኙልን በትህትና እንጠይቃለን። በእለቱም ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ያለውን ጨዋታ አብረን የምናይ ይሆናል። አድራሻ:ፒያሳ ሰባ ደረጃበዋናነት የሚያስፈልጉዋቸው  ዝርዝር ነግረውናል
1,የምግብ ዘይት
2,እንቁላል
3.ወተት
4,ጤፍ
5,አሮጌ ልብሶች
6,ሌሎች ምስር መኮሮኒ ፖስታ… አስቤዛዎችለተጨማሪ መረጃ
+251944309760 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ
(ዝርዝር ፕሮግራሙን ቀኑ ሲቃረብ ከነ ሰዓቱ ይፋ እናደርጋለን)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Social media & sharing icons powered by UltimatelySocial